Introduction to Financial Networking Business
መግቢያ
በሀገራችን በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የሀብት ልዩነት እንዳለ ይታወቃል በመሆኑም አብዛኛውን ቁጥር የሚይዘው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የሕብረተሰብ ክፍል የኑሮ ውድነቱንና ጠቅላላ የኢኮኖሚ ጫናውን ቀንበር ተሸክሞ ይኖራል በአንፃሩ ጥቂት የሚሆኑት ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ገቢያቸው እየጨመረ እና የኢኮኖሚ ጫናው እንደ መልካም አጋጣሚ የሚሆንላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎችም አሉ፡፡ስለሆነም ይህንን የተጋነነ የሀብት ልዩነት በማመጣጠን ሁሉም ተጠቀሚ የሚሆንበትንና የኢኮኖሚ ጫናውን መሸከም የሚችልበትን ሥርዓት ለመፍጠር ታስቧል፡፡ይህንን የብዙዎች ጥያቄና ችግር በቀላሉ የሕብረትን ኃይል በመጠቀም መፍታት የሚቻለ ሲሆን ይህንን ኃይል የሚጠቀም አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት የሐብት ልዩነቱ እየሰፋና ብዙዎች ለችግር እየተጋለጡ ጥቂቶች ደግሞ ያለመጠን እየከበሩ ሲሄዱ ቆይቷል ስለዚህ ሁሉንም አካላት ማለትም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንም ከፍተኛ ገቢ ያላቸውንም የሕብረተሰብ ክፍሎች በማቀራረብ እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ እርስ በርስ በሕብረት፣በታማኝነትና በአንድነት የሚያሳድግ አዲስ ሥርዓት በማስፈለጉ ይህ ድርጅት ይህንን ከዕለት ተዕለት የኑሮ ወጪያችን ጋር የሚያያዝ ፋይናሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ (Finacial Networking Business (FNB)) የተሰኘ አዲስ ሥርዓት ይዞ መጥቷል፡፡ይህ ሥርዓት በጊዜ እና በቦታ ሳይወሰን የሰዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ከፍተኛ የሆነ የሀብት ልዩነትን ለማስቀረት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ወደፊት በእያንዳንዱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ሥርዓቱን በመዘርጋት የሐብት ልዩነቶችን በማጥበብ ብዙዎች የሚጠቀሙበት የኑሮ ደረጃቸውንም የሚያሻሽሉበት ሁኔታን ይፈጥራል፡፡
ፋይናሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ (FINACIAL NETWORKING BUSINESS (FNB))
ይህ ሥርዓት ጊዜ ፣ ቦታና የገቢ መጠን የማይወስነው ሁሉንም አካታች የሆነ ቀላል ሥርዓት ነው፡፡ብዙዎቻችን ኑሮአችንን ለማሻሻልና ገቢያችንን ለማሳደግ እናስባለን ብዙ ዓይነት ቢዝነሶችንም ለመጀመር እናስባለን ነገር ግን ብዙ ጊዜ እንቅፋት የሚሆንብን ነገር የግል ስራችንን ሆነ ሌሎች የቢዝነስ ዘርፎችን ለመጀመር የሚያስችል የገንዘብ አቅም አለመኖር ነው ይሁን እንጂ ይህ ለብቻችን የከበደን ነገር በሕብረት ሲሆን ቀላል ይሆናል፡፡እዚህ ላይ ለምሳሌነት የምንጠቅሰው ለብዙ ጊዜያት ስንጠቀምበት የነበረውን ጠቃሚ ሥርዓታችን የሆነውን ዕቁብን ማንሳት እንችላለን በዚህ ሥርዓት ውስጥ ትንሽ ገቢ ያለው ሰው በአቅሙ ዕቁብ በመጣል ከዕቁቡ አባላት ተሰብስቦ አንድ ላይ በሚደርሰው ገንዘብ በገቢው ውስንነት የተነሳ በአንዴ ማድረግ የማይችለውን ነገር ማድረግ ይችላል ማለት ነው፡፡ስለሆነም ይህንን ሕብረትና አንድነት የሚሰጠንን ኃይል ተጠቅመን እያንዳንዳችን የምንፈልገውን ነገር ማሳካት እንችላለን ማለት ነው፡፡ስለዚህ ድርጅታችን ፋይናሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ ይህንን ፋይናሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ የተሰኘ ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት በቀላሉ ሊጀመር በሚችል መልኩ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል ሊያካትት በሚችል መልኩ በትንሽ የፋይናሺያል ኔትዎርክ መገንቢያ የካፒታል መጠን እና አነስተኛ ዕለታዊ ወይም ወርሀዊ የኑሮ ወጪ ፍጆታ ላይ የሚያተኩር ሥርዓት በማስጀመር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች የኑሮ ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ለማድረግ ታስቧል፡፡ይህ ሥርዓት የሚፈጥረው የቢዝነስ ዘርፍ በዓይነቱ ለየት ያለ እና ለመጀመርም ስራውንም ለመስራት እጅግ በጣም ቀላል የሆነ ሲሆን ስለስራው ምንነት ፣ ስራውን ለመጀመር ስለሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እና ስለ አጠቃላይ የስራው ሂደቱ ትንታኔ ከታች በዝርዝር ተቀምጧል፡፡
1.ስለ ስራው ምንነት፡- ሰራው ማንኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ያለ ሰው ሊሰራው የሚችል እንዲሁም በቦታ እና በጊዜ የማይወሰን የትም ቦታ ሆነው የሚሰሩት ስራ ሲሆን በዋናነት ስራው ፋይናሺያል ኔትዎርክ መገንባት ነው፡፡ይህም ማለት ከሰዎች ጋር ትስስር በመፍጠር የካፒታል መጠንን ማሳደግ ማለት ነው ለዚህም ሁነኛ ምሳሌ ሊሆነን የሚችለው ከላይ የጠቀስንው የሀገራችን ሥርዓት ዕቁብ ነው፡፡ስለዚህ ይህንን በጣም ጠቃሚ ሥርዓታችንን በማዘመን እና የተለያዩ የክፍያና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን በመጨመር እንዲሁም በቀላሉ ለሁሉም እንደየ አቅሙ ተደራሽ በማድረግ የሥርዓቱ ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡
2.ስራውን ለመጀመር ስለሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ፡- ስራውን ለመጀመር ወይም በፋይናሺያል ኔትዎርክ ውስጥ በመቀላቀል የራስን ፋይናሺያል ኔትዎርክ በመፍጠር ከጥቅሙ ተካፋይ ለመሆን ማንኛውም ሰው ባለው የገቢ ልክ ተሳታፊ መሆን ይችላል፡፡ስለዚህ ስራውን ለመጀመር የሚፈልግ ሰው ከታች የተገለፀውን የስራ ሂደቱን ትንታኔ በመረዳት ድርጅቱ የሚያዘጋጀውን ቅፅ በመሙላት መመዝገብ የሚችል ይሆናል።
3.አጠቃላይ የስራው ሂደቱ ትንታኔ፡- አንድ ግለሰብ በመጀመሪያ ድርጅቱ ባዘጋጀው ኦላይን የመመዝገቢያ መንገድ መረጃዎችን በመላክ ወይም በድርጅቱ የመመዝገቢያ ቅፅ (Registration Form) አማካኝነት መረጃዎችን በመሙላት በድርጅቱ ኢሜል ወይም በድርጅቱ የቴሌግራም አካውንት የመመዝገቢያ ቅፁን በመላክ ይመዘገባል ድርጅቱም በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የFNB ሥርዓት ለመጀመር የሚያስችለውን የመለያ ቁጥር በአጭር የፅሁፍ መልዕከት (Message) የሚልክ ሲሆን እንዲሁም ለግለሰቡ FNB ሥርዓት ግንባታ የሚረዱትን የድርጅቱ ማህተም ያረፈባቸውን የመመዝገቢያ ቅፅና ስለ ስራ ሂደቱ ዝርዝር ትንታኔ የሚሰጡ መረጃዎችን በሙሉ በድርጅቱ ኢሜል ወይም የቴሌግራም ፔጅ የሚልክ ይሆናል፡፡ይህ ግለሰብ የ FNB ሥርዓቱን ከ 200 ብር ወርሀዊ የካፒታል መጠን ጀምሮ መገንባት ይችላል ስለሆነም ግለሰቡ ከላይ እንደተገለፀው የምዝገባ ሂደቱን ሲጨርስ የድርጅቱ ወኪል (Agent) ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለዚህ አንድ ሰው የ FNB ሥርዓቱን እንዴት መገንባት እንደሚችል እና ከ FNB ሥርዓቱ ስለሚያገኛቸው ክፍያ በዝርዝር እንመልከታለን።
በፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ውስጥ የአከፋፈል ሥርዓቱ ወጥ ፣ ግልፅ እና ፍትሀዊ ነው፡፡በመሆኑም አንድ ወኪል የሚከፈለው የክፍያ መጠን ቢዝነሱን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ፋይናንሺያል ኔትዎርኩን ገንብቶ እስኪጨርስ እና ከጨረሰም በኋላ ከስሩ ከሚኖረው ወይም ከሚጠራቀመው ጠቅላላ የካፒታል መጠን ላይ 10 በመቶ ያክሉን ነው፡፡ እንዲሁም 50 በመቶ የሚሆነውን የወርሀዊ የካፒታል መጠኑ ለሞባይል ካርድ የሚቀመጥለት ሲሆን ቀሪው 40 በመቶ የሚሆነው የካፒታል መጠን ደግሞ እንደየድርሻቸው ወኪሉ በገነባው የፋይናንሺል ኔትዎርክ ስር ላሉ ሰዎች የሚከፈል ይሆናል፡፡ስለዚህ የአከፋፈል ሥርዓቱን በዝርዝር ለማሳየት እንዲረዳን በምሳሌ አስደግፈን እናሳይ አንድ ግለሰብ የፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነሱን በ 200 ብር ወርሀዊ የካፒታል መጠን ቢጀምር እና በቀጣይ የመለያ ቁጥሩን ተጠቅሞ የፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነሱ መሠረት የሚሆኑትን 5 ሰዎች በማስመዝገብ መሠረቱን ቢጥል እዚህ ደረጃ ላይ የሚኖረውን የክፍያ ሥርዓት ስንመለከት፡-
የአንድ ሰው ወርሀዊ የካፒታል መጠን = 200 ብር
ጠቅላላ የሰዎች ብዛት = 5
ጠቅላላ የካፒታል መጠን = 5x200 = 1,000 ብር
የክፍያ መጠን (10 በመቶ) = 1,000x10% = 100 ብር
ለሞባይል ካርድ የሚቀመጥ የገንዘብ መጠን (50 በመቶ) = 200 x 50% = 100 ብር
ጠቅላላ ክፍያ = 100+100 = 200ብር
ከዚህ በመቀጠል አዲሶቹ 5 ሰዎች እያንዳንዳቸው ለፋይናንሺያል ኔትዎርካቸው መሠረት የሚሆኑዋቸውን 5 ሰዎች ወደ ኔትዎርኩ ሲያስገቡ 5 x 5 = 25 ይሆናሉ፡፡እዚህ ደረጃ ላይ ያለውን የክፍያ ሥርዓት ስንመለከት፡-
የአንድ ሰው ወርሀዊ የካፒታል መጠን = 200 ብር
ጠቅላላ የሰዎች ብዛት = 5+25 = 30
ጠቅላላ የካፒታል መጠን = 30x200 = 6,000 ብር
የክፍያ መጠን (10 በመቶ) = 6,000x10% = 600 ብር
ለሞባይል ካርድ የሚቀመጥ የገንዘብ መጠን (50 በመቶ) = 200 x 50% = 100 ብር
ጠቅላላ ክፍያ = 600+100 = 700ብር
አሁንም በመቀጠል አዲሶቹ 25 ሰዎች እያንዳንዳቸው ለፋይናንሺያል ኔትዎርካቸው መሠረት የሚሆኑዋቸውን 5 ሰዎች ወደ ኔትዎርኩ ሲያስገቡ 25 x5 = 125 ይሆናሉ፡፡እዚህ ደረጃ ላይ ያለውን የክፍያ ሥርዓት ስንመለከት፡-
የአንድ ሰው ወርሀዊ የካፒታል መጠን = 200 ብር
ጠቅላላ የሰዎች ብዛት = 5+25+125 = 155
ጠቅላላ የካፒታል መጠን = 155x200 = 31,000 ብር
የክፍያ መጠን (10 በመቶ) = 31,000x10% = 3,100 ብር
ለሞባይል ካርድ የሚቀመጥ የገንዘብ መጠን (50 በመቶ) = 200 x 50% = 100 ብር
ጠቅላላ ክፍያ = 3,100+100 = 3,200ብር
አሁንም በመቀጠል አዲሶቹ 125 ሰዎች እያንዳንዳቸው ለፋይናንሺያል ኔትዎርካቸው መሠረት የሚሆኑዋቸውን 5 ሰዎች ወደ ኔትዎርኩ ሲያስገቡ 125 x5 = 625 ይሆናሉ፡፡እዚህ ደረጃ ላይ ከላይ በምሳሌነት የጠቀስንው ግለሰብ ፋይናንሺያል ኔትዎርኩን ገንብቶ ይጨርሳል ማለት ነው፡፡ሌሎች በስሩ ያሉት ሰዎች ደግሞ ልክ እንደርሱ ፋይናንሺያል ኔትዎርካቸውን በጊዜ ሂደትና በመተካካት ገንብተው ይጨርሳሉ ማለት ነው፡፡እዚህ ደረጃ ላይ ያለውን የክፍያ ሥርዓት ስንመለከት፡-
የአንድ ሰው ወርሀዊ የካፒታል መጠን = 200 ብር
ጠቅላላ የሰዎች ብዛት = 5+25+125+625 = 780
ጠቅላላ የካፒታል መጠን = 780x200 = 156,000 ብር
የክፍያ መጠን (10 በመቶ) = 156,000x10% = 15,600 ብር
ለሞባይል ካርድ የሚቀመጥ የገንዘብ መጠን (50 በመቶ) = 200 x 50% = 100 ብር
ጠቅላላ ክፍያ = 15,600+100 = 15,700ብር
ወኪሉ ፋይናንሺያል ኔትዎርኩን ከላይ ባየንው ምሳሌ መሠረት ገንብቶ ከጨረሰ የክፍያ መጠኑ ከፍተኛ የሚሆን ሲሆን ገንብቶ ባይጨርስም ግን በተጠራቀመው የካፒታል መጠን ልክ 10 በመቶ የሚሆነውን በቀጥታ የሚከፈለው ይሆናል፡፡ስለዚህ በዚህ ምሳሌ መሰረት ሁላችሁም የራሳችሁን ክፍያ መጠን ማስላት የምትችሉ ሲሆን ሁልጊዜ በየወሩ ድርጅቱ ክፍያ ከመፈፀሙ በፊት የሁሉንም ወኪል ደንበኞች መረጃ በዝርዝር ለእያንዳንዱ ወኪል ያሳውቃል ማለትም ወኪሉ በገነባው ፋይናንሺያል ኔትዎርክ ስር ያሉ ሰዎችን ዝርዝር ፣ የእያንዳንዱን በፋይናንሺያል ኔትዎርኩ ሥር ያሉ ሰዎችን ወርሀዊ የካፒታል መጠን እንዲሁም የወኪሉን የክፍያ መጠን የሚያሳይ ዝርዝር እና ግልፅ መረጃ በየወሩ ስለሚደርሰው ከላይ ባለው ምሳሌ መሠረት የሚከፈላችሁን የክፍያ መጠን በግልፅ አስልታችሁ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ስለዚህ ወኪሉ በዚህ ሁኔታ በገነባው የ FNB ሥርዓት አማካኝነት የወር ገቢውን ሠንጠረዡ ላይ በተገለፀው መልኩ ማሳደግ የሚችል ይሆናል ማለት ነው፡፡ስለሆነም ማንኛውም ወኪል ወደ FNB ሥርዓቱ ከተቀላቀለ እና የ FNB ሥርዓቱን ገንብቶ ከጨረሰ በኋላና በመገንባት ላይ እያለ በ FNB ሥርዓቱ አማካኝነት የሚገኘውን ወርሀዊ ገቢ ቀጣይ እንዲሆን ለማድረግ ሲመዘገብ የጀመረውን ወርሀዊ የካፒታል መጠንና የአገልግሎት ክፍያ በየወሩ ገቢ ማድረግ ሲኖርበት እዚህ ላይ የአሠራር መንዛዛትና ድግግሞሽን ለማስቀረት ድርጅቱ ከሲስተሙ ላይ ተቆራጭ የሚደይኖርበታል ድርጅቱም ይህንን በማረጋገጥ ወር በገባ ከ5-15 ባሉት ቀናት ውስጥ ወኪሉ ከገነባው የ FNB ሥርዓት የሚያገኘውን ጠቅላላ ወርሀዊ ክፍያ በወኪሉ የባንክ አካውንት ያስገባል ማለት ነው፡፡ወኪሉም ለድርጅቱ ከወርሀዊ የካፒታል መጠኑ ጋር አንድ ላይ በማድረግ የአገልግሎት ክፍያ (Service fee) 35 ብር የሚከፍል ይሆናል እዚህ ላይ የካፒታል መጠናቸውን 500 ብርና ከዛ በላይ በማድረግ የ FNB ሥርዓት ግንባታቸውን ለሚጀምሩ የአገልግሎት ክፍያ (Service fee) የካፒታል መጠናቸውን 10 በመቶ ያክል ይሆናል ማለት ነው ፡፡ሌላው ወኪሉ ሥራውን ለመጀመር ከላይ የተገለፁትን በሙሉ አሟልቶ ሲመዘገብ የካፒታል መጠኑንና ሌሎች መረጃዎችን ያከተተ የሥራ ስምምነት ማስረጃ ከድርጀቱ ይላክለታል ይህም የሥራ ስምምነት ማስረጃ ወኪሉ ከድርጅቱ ጋር በመሆን ለሚሰራው የፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ስራ ማረጋገጫ የግል ሠነዱ ይሆናል ማለት ነው፡፡በተጨማሪ እንዲሁም ወኪሉ በሚገነቡት ፋይናንሺያል ኔትዎርክ ውስጥ የሚከናወኑትን ማናቸውንም ለውጦች ማለትም በፋይናንሺያል ኔትዎርኩ ውስጥ የተካተቱትን የሰዎች ዝርዝር ፣ የእያንዳንዱን ወርሀዊ የካፒታል መጠን ፣ ጠቅላላ የካፒታል መጠን ፣ ጠቅላላ ወርሀዊ ክፍያን እና ሌሎች ከዚህ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በየወሩ ድርጅቱ ለወኪሉ የሚያሳውቅ ሲሆን በቀጣይነት ወርሀዊ የካፒታል መጠን ክፍያውን የማይፈፅም ሰው ከ FNB ሥርዓቱ ውስጥ የሚወጣ ሲሆን በቆይታው ከ FNB ሥርዓቱ የሚያገኘውን ክፍያ እና ተቀማጭ 50 በመቶ የካፒታል መጠን የመውሰድ ሙሉ መብት ያለው በመሆኑ ገንዘቡ የሚከፈለው ይሆናል፡፡
አሪፊ
ReplyDeleteAlright! Thank you too much!!!
Deleteህብረት ፣ አንድነትና መተጋገዝን የማይወድ ይኖራል ብየ አላስብም ግን ስለደህንነቱ ሁኔታ እንዴት ማረጋገጥ እንደምንችል አሁንም ተጨማሪ መረጃ የሚያስፈልግ ይመስለኛል።አመሰግናለው
ReplyDeleteህጋዊ መሆናቹ ማረጋገጫ ስጡን
ReplyDeleteAlright! we are happy to help you!
DeleteYou can have detailed explanation from our Telegram page as well as in person at A.A around Bethel Square in front of Familiy Tower.
For additional information :
phone no: 0978900505
ስራው ጥሩ ቢሆንም አድራሻችሁ ህጋዊነታችሁን የሚያሳይ ሰነድ ብታሳዩን ልክ እንደሌሎቹ ብሩን ሰብስባችሁ ብትጠፉስ ከዚህ በፊት የታየ ነገር ስላለ
ReplyDeleteAlright! You can have detailed information from our Telegram page as well as in person at A.A around Bethel Square!
DeleteWe are Happy to help you.
Thank you.
አረፍ ነዉ
ReplyDelete