Posts

Showing posts from April, 2022

Company Structure and Formation

              የድርጅቱ አወቃቀርና አመሠራረት ሀገር በቀል ድርጅታችን ፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ በሕብረት፣በታማኝነትና በአንድነት ላይ የተመሠረተ የሰፊውን ሕዝብ ችግር በሕብረት ሊፈታ የሚችል ፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ የተሰኘ የዜጎችን የካፒታል አቅም በማሳደግ ወደ ንግዱ ሥርዓት የሚቀላቅልና የተሻለ የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩ የሚረዳ አላማ በመያዝ በመላዉ ኢትዬጵያ የሚተገበር መሪ ዕቅድ በመንደፍ አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል፣በዞን አንዲሁም ወረዳ ድረስ በመውረድ ስራውን ተደራሽ እያደረገ ይገኛል።ድርጅታችን በአዋጅ ቁጥር 980/2008 ዓ.ም መሠረት ከመንግስት ፍቃድ በማውጣት ሕጋዊ ሠውነት ኖሮት በይፋ የተመሠረተበት ቀን ታህሳስ 04/2014 ዓ.ም ሲሆን የድርጅቱ ባለቤቶችና መስራቾች እንዲሁም የድርጅቱ መሪና አስተዳዳሪዎች፦ 1.አቤል አበበ ተክለፃዲቅ 2.ይዲድያ ደረጀ ተረፈ ሲሆኑ የተለያየ የሙያ ባለቤት በሆኑ ሲኒየር ፕሮሞተሮችና ጁኒየር ፕሮሞተሮች የተዋቀረም ነው በዋናነት ሁሉንም አቃፊ የሆነ ሲስተምን መሠረት ያደረገ አሠራርን ይከተላል።ራዕያችን የሁሉንም ሀሳብ አሳታፊ በማድረግ በሕብረት ላይ ጠንካራ መሠረትን በመገንበት ሀገራችንንና ዜጎቿን ወደ ከፍታ ማማ ላይ ማውጣት  ነው። በሕብረት፣በታማኝነትና በአንድነት እጅለእጅ ተያይዘን ወደ ከፍታ እንጓዝ!!!     ፋይናንሺያል ኔትወርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ                                               ...

Aim of Financial Networking

ሀገር በቀል ድርጅታችን ፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ የዘረጋው ፋይናንሺል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ዝርዝር አላማዎች፡- 1.አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ የሚሆኑበትን የቢዝነስ ዘርፍ መዘርጋት ፣ 2.በስፋት በሀገራችን ያለውን ጥቂቶች ብቻ የሚጠቀሙበትን የቢዝነስ ሥርዓት በመቀየር ሁሉንም በተዋረድ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓት መገንባት ፣ 3.ከዚህ በፊት በተለያዩ ካምፓኒዎች ተሞክሮ ጥቂት ሰዎችን ብቻ በመጥቀም አብዛኛውን ሰው ከጥቅም ተካፋይነት ውጪ ሲያደርግ የነበረውን በኔትዎርክ ግንባታ ላይ የክፍያ ሥርዓቱን  ፍትሀዊ እንዳይሆን የሚያደርገውን ገደብ የለሽ ሥርዓት (Pyramidal System) በማስወገድና ገደብ በማበኘት ቀድመው ወደ ኔትዎርኩ የገቡ ሰዎች ብቻ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ አስቀርቶ በየጊዜው ወደ ኔትዎርክ ሥርዓቱ የሚቀላቀሉትን ሰዎች ከክፍያ ሥርዓቱ ተጠቃሚ በማድርግ የተመጣጠነ እና ፍትሀዊ የክፍያ ሥርዓትን መዘርጋት፣ 4.በአሁኑ ሠዓት እየተሸረሸሩ ያሉትን እንደ ዕቁብ የመሳሰሉትን የሀገራችን የኢትዮጵያ ጠቃሚ ሥርዓቶችን በማዘመንና የመተባበር ባህላችንን በማሳደግ አንድ ሰው የሚያድግበትን ሥርዓት አስቀርቶ ሁሉም በሕብረት ፣ በታማኝነትና በአንድነት የሚያድግበትን ፍትሃዊ ሥርዓት መፍጠር ፣ 5.የተለያየ የገቢ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመጀመር የሚያስቧቸው ነገርግን በካፒታል ውስንነት የተነሳ ያልሰሯቸውን የቢዝነስ ዘርፎች እንዲጀምሩ የሚረዳቸውን የካፒታል መጠን እንዲያገኙ ማድረግ እንዲሁም ድርጅታችን ወደፊት ይህንን ፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ሥርዓት ወደተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ በሚያስጀምርበት ወቅት በፋይናንሺያል ኔትዎርክ ውስጥ የታቀፉ ሰዎችን ወደ ንግድ ሥርዓቱ በማስገባት በሚፈልጉት የንግድ ዘርፍ ላይ አሰማርቶ ሊሰርቱ ...

Introduction to Financial Networking Business

                            መግቢያ            በሀገራችን በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ውስጥ ከፍተኛ የሀብት ልዩነት እንዳለ ይታወቃል በመሆኑም አብዛኛውን ቁጥር የሚይዘው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የሕብረተሰብ ክፍል የኑሮ ውድነቱንና ጠቅላላ የኢኮኖሚ ጫናውን ቀንበር ተሸክሞ ይኖራል በአንፃሩ ጥቂት የሚሆኑት ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ገቢያቸው እየጨመረ እና የኢኮኖሚ ጫናው እንደ መልካም አጋጣሚ የሚሆንላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎችም አሉ፡፡ስለሆነም ይህንን የተጋነነ የሀብት ልዩነት በማመጣጠን ሁሉም ተጠቀሚ የሚሆንበትንና የኢኮኖሚ ጫናውን መሸከም የሚችልበትን ሥርዓት ለመፍጠር ታስቧል፡፡ይህንን የብዙዎች ጥያቄና ችግር በቀላሉ የሕብረትን ኃይል በመጠቀም መፍታት የሚቻለ ሲሆን ይህንን ኃይል የሚጠቀም አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት የሐብት ልዩነቱ እየሰፋና ብዙዎች ለችግር እየተጋለጡ ጥቂቶች ደግሞ ያለመጠን እየከበሩ ሲሄዱ ቆይቷል ስለዚህ ሁሉንም አካላት ማለትም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውንም ከፍተኛ ገቢ ያላቸውንም የሕብረተሰብ ክፍሎች በማቀራረብ እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ እርስ በርስ በሕብረት፣በታማኝነትና በአንድነት የሚያሳድግ አዲስ ሥርዓት በማስፈለጉ ይህ ድርጅት ይህንን ከዕለት ተዕለት የኑሮ ወጪያችን ጋር የሚያያዝ ፋይናሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ (Finacial Networking Business (FNB)) የተሰኘ አዲስ ሥርዓት ይዞ መጥቷል፡፡ይህ ሥርዓት በጊዜ እና በቦታ ሳይወሰን የሰዎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻልና ከፍተኛ የሆነ የሀብት ልዩነትን ለማስቀረት ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ወደፊት በእያንዳንዱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ሥ...

Registration Process

 ሀገር በቀል ድርጅታችን ፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ በአዋጅ ቁጥር 980/2008ዓ.ም መሠረት ከመንግስት ፍቃድ አውጥቶ ዋና መቀመጫዉን አዲስ አበባ ላይ በማድረግ በመላዉ ኢትዮጵያ ላይ ኔትዎርኩን ዘርግቶ በሕብረት የዜጎችን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ መጠነ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው። በመሆኑም ሕጋዊ የድርጅቱ አባል በመሆን በወኪልነት በመላው ኢትዬጵያ በonline በመስራት በሕብረት ገቢያችሁን ማሳደግ ለምትፈልጉ ሁሉ ከድርጅቱ የተሰጠ ቅደም ተከተላዊ መግለጫ:- 1) የድርጅቱን አላማ በግልፅ መረዳት፣ 2) በቀጥታ የድርጅቱን ወኪሎች ወይም ፕሮፌሽናል ፕሮሞተሮች በማነጋገር የወኪል መለያ ቁጥር (Id.no) እና የወኪሉን/የፕሮሞተሩን ሙሉ ስም መመዝገብ 3) የመነሻ የካፒታል መጠንን ከብር 200 እና የአገልግሎት ክፍያ (Service fee) ብር 35 በመመዝገቢያ ቅፁ ላይ በተገለፀው የድርጅቱ የባንክ አካውንት ቁጥር በሞባይል ባንኪንግ ወይም በቀጥታ በባንክ ገቢ ማድረግ የካፒታል መጠን ከብር 500 እና ከዛ በላይ ተመዝጋቢዎች የአገልግሎት ክፍያ (Service fee) የካፒታል መጠንን 10 በመቶ ነው፣ 4) የሞሉትን የመመዝገቢያ ቅፅ ፣ ክፍያ የፈፀሙበትን የሞባይል ባንኪንግ ማረጋገጫ ወይም የባንክ ደረሰኝ (Slip) መረጃና ማንነቶን የሚገልፅ ሕጋዊ መታወቂያ ፎቶ በማንሳት በመመዝገቢያ ቅፁ ላይ በተገለፀው የድርጅቱ የቴሌግራም ወይም የኢሜል አድራሻ ላይ መላክ ወይም በቀጥታ በድርጅቱ ኦንላይን መመዝገቢያ መንገድ የግል መረጃዎችን በመሙላትና የባንክ መረጃንና የመታወቂያን ፎቶ መላክ 5) ድርጅቱም ከላይ የተገለፁት መስፈርቶች መሟላታቸውን በማረጋገጥ በመላው ኢትዬጵያ ላይ ሥራዎትን እንዲጀምሩ የሚያስችሎትን የግል መለያ ቁጥር (Id.no) ፣ ስለ...