Aim of Financial Networking

ሀገር በቀል ድርጅታችን ፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ የዘረጋው ፋይናንሺል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ዝርዝር አላማዎች፡-

1.አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ የሚሆኑበትን የቢዝነስ ዘርፍ መዘርጋት ፣

2.በስፋት በሀገራችን ያለውን ጥቂቶች ብቻ የሚጠቀሙበትን የቢዝነስ ሥርዓት በመቀየር ሁሉንም በተዋረድ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሥርዓት መገንባት ፣

3.ከዚህ በፊት በተለያዩ ካምፓኒዎች ተሞክሮ ጥቂት ሰዎችን ብቻ በመጥቀም አብዛኛውን ሰው ከጥቅም ተካፋይነት ውጪ ሲያደርግ የነበረውን በኔትዎርክ ግንባታ ላይ የክፍያ ሥርዓቱን  ፍትሀዊ እንዳይሆን የሚያደርገውን ገደብ የለሽ ሥርዓት (Pyramidal System) በማስወገድና ገደብ በማበኘት ቀድመው ወደ ኔትዎርኩ የገቡ ሰዎች ብቻ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ አስቀርቶ በየጊዜው ወደ ኔትዎርክ ሥርዓቱ የሚቀላቀሉትን ሰዎች ከክፍያ ሥርዓቱ ተጠቃሚ በማድርግ የተመጣጠነ እና ፍትሀዊ የክፍያ ሥርዓትን መዘርጋት፣

4.በአሁኑ ሠዓት እየተሸረሸሩ ያሉትን እንደ ዕቁብ የመሳሰሉትን የሀገራችን የኢትዮጵያ ጠቃሚ ሥርዓቶችን በማዘመንና የመተባበር ባህላችንን በማሳደግ አንድ ሰው የሚያድግበትን ሥርዓት አስቀርቶ ሁሉም በሕብረት ፣ በታማኝነትና በአንድነት የሚያድግበትን ፍትሃዊ ሥርዓት መፍጠር ፣

5.የተለያየ የገቢ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ለመጀመር የሚያስቧቸው ነገርግን በካፒታል ውስንነት የተነሳ ያልሰሯቸውን የቢዝነስ ዘርፎች እንዲጀምሩ የሚረዳቸውን የካፒታል መጠን እንዲያገኙ ማድረግ እንዲሁም ድርጅታችን ወደፊት ይህንን ፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ሥርዓት ወደተለያዩ የንግድ ዘርፎች ላይ በሚያስጀምርበት ወቅት በፋይናንሺያል ኔትዎርክ ውስጥ የታቀፉ ሰዎችን ወደ ንግድ ሥርዓቱ በማስገባት በሚፈልጉት የንግድ ዘርፍ ላይ አሰማርቶ ሊሰርቱ የሚያስቡት የቢዝነስ ባለቤት ማድረግ ነው።

 ሀገር በቀል  ድርጅታችን ፋይናንሺያል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ በሕብረት ፣ በታማኝነትና በአንድነት እጅለእጅ ተያይዘን ወደ ከፍታ እንጓዝ በሚል መሪ ቃሉ ሀገራችን ኢትዮጵያን እናሳድግ ብሎ የተነሳ ሲሆን ይህ ደግሞ የሚሆነው የዜጎችን ገቢ በማሳደግ እና የኑሮ ደረጃቸውን ከፍ በማድረግ ስለሆነ ይህንን የዜጎችን ገቢና የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽል ፋይናንሺል ኔትዎርኪንግ ቢዝነስ የተሰኘ ሥርዓት በሕብረት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

እኛ ኢትዮጵያዊያን አብረን መብላት ብቻ ሳይሆን አብረን መስራትም እናውቅበታል!!!

ዘመኑ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን የከፍታ ዘመን ነው!!!

በሕብረት፣በታማኝነትና በአንድነት እጅለእጅ ተያይዘን ወደ ከፍታ እንጓዝ!!!      

     ፋይናንሺያል ኔትወርኪንግ ቢዝነስ ግሩፕ                                                                                                                           

Comments

Popular posts from this blog

Company Structure and Formation

Registration Process